የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ይህን ያስታወቀው የሀገርን ሉአላዊነት ለማስከበር ለተሰማራው መከላከያ ሰራዊትና ከፍተኛ ተሳትፎ እያደረጉ ላሉ የክልል ልዩ ኃይሎችና የአካባቢ ሚሊሺያዎች የሚያደርጉትን ተጋድሎ መደገፉን አስመልክቶ ነሀሴ 23 ቀን 2013 ዓ.ም በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ነው። በተገባደደው 2013 ዓ.ም በተለያዩ የባንክ አገልግሎት ዘርፎች የተሻለ አፈፃፀም የተመዘገበበት እንደነበር ያስታወቁት የባንኩ ፕሬዚዳንት አቶ አቤ ሳኖ ከ140 ቢሊዮን ብር በላይ የተቀማጭ ገንዘብ መጠን በማሰባሰብ በታሪኩ ከፍተኛ የተባለውን ውጤት ማሳካት የቻለበት ዓመት ነበረም ነው ያሉት። በተያዘው አዲስ በጀት አመት ሐምሌ ወርም በተለያዩ የባንክ አገልግሎቶች አበረታች ውጤት እያስመዘገበ ነው ያሉት አቶ አቤ በዚህም የባንኩ አጠቃላይ ሀብት 1.1 ትሪሊዮን ብር ደርሷል።

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የ800 ሚሊዮን ብር ድጋፍ ማድረጉን አስታወቀ። ባንኩ አጠቃላይ ሀብቱ 1 ነጥብ 1 ትሪሊዮን ብር ሀብት መድረሱንም ገልጿል። ========================================= የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ይህን ያስታወቀው የሀገርን ሉአላዊነት ለማስከበር ለተሰማራው መከላከያ ሰራዊትና ከፍተኛ ተሳትፎ እያደረጉ ላሉ የክልል ልዩ ኃይሎችና የአካባቢ ሚሊሺያዎች የሚያደርጉትን ተጋድሎ መደገፉን አስመልክቶ ነሀሴ 23 ቀን 2013 ዓ.ም በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ነው። በተገባደደው 2013 ዓ.ም በተለያዩ የባንክ አገልግሎት ዘርፎች የተሻለ አፈፃፀም የተመዘገበበት እንደነበር ያስታወቁት የባንኩ ፕሬዚዳንት አቶ አቤ ሳኖ ከ140 ቢሊዮን ብር በላይ የተቀማጭ ገንዘብ መጠን በማሰባሰብ በታሪኩ ከፍተኛ የተባለውን ውጤት ማሳካት የቻለበት ዓመት ነበረም ነው ያሉት። በተያዘው አዲስ በጀት አመት ሐምሌ ወርም በተለያዩ የባንክ አገልግሎቶች አበረታች ውጤት እያስመዘገበ ነው ያሉት አቶ አቤ በዚህም የባንኩ አጠቃላይ ሀብት 1.1 ትሪሊዮን ብር ደርሷል። ይህም ባንኩ በምስራቅና መካከለኛው አፍሪካ ካሉ ባንኮች መካከል ትሪሊዮን ሀብትን በመፍጠር ሁለተኛው ባንክ እንዳደረገው አስታውቀው ባንኩ ትሪሊዮን ሀብት ከተሻገሩ ጥቂት አፍሪካዊ ባንኮች ምድብ ውስጥ በመቀላቀሉ እንኳን ደስ አላችሁም ነው ያሉት። የትሪሊዮን ሀብት መጠንን የተሻገረው ባንኩ የ80ኛ ዓመት ምስረታ እና የዋና መስሪያ ቤት ህንፃ ገንብቶ በማጠናቀቅ ላይ ባለበት ሰዓት መሆኑ ታሪካዊ ግጥምጥሞሽ እንደፈጠረም ነው አቶ አቤ የገለፁት። ትሪሊዮን ሀብት መሻገሩ በሀገር ውስጥ ያለውን የባንክ ዘርፍ የመሪነት ሚና ከማጠናከር ባሻገር በቀጠናው ለሚያደርገው የባንክ አገልግሎት ማስፋፋት እና ተደራሽነት ለማረጋገጥና ለመላው ህብረተሰብ የላቀ የባንክ አገልግሎት ለመስጠት ብርታት እንደሚሆንም አስታውቀዋል። በሩቅ ይታይ የነበረውን የትሪሊዮን ሀብት መጠን ማሳካት የተቻለው ከህዝቡ ጋር ሆነው በሰሩት ስራ መሆኑን አስታውሰው ሁለተኛውን ትሪሊዮን ለመድረስ ግን ጥቂት አመታት ግን ብዙ ስራዎች ይጠበቁብናልም ነው ያሉት። በእነዚህ አመታት ውስጥ በባንክ ዘርፍ ከተመዘገቡ መልካም ውጤቶች በተጨማሪ በመላ ሃገሪቱ ለሚከናወኑና ኢትዮጵያን ወደ ከፍታ ለማድረስ በርካታ ፕሮጀክቶች ላይ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ድጋፍና ተሳትፎ እጅግ ጉልህ መሆኑም ነው የተገለፀው። በባንክ ዘርፍ ያስመዘገበውን መልካም አፈፃፀም በማህበራዊ ልማት ዘርፉ አጠናክሮ መቀጠሉን ያስታወቁት አቶ አቤ በተለይ ከሚያገኘው ትርፍ ላይ የተለያዩ ማህበራዊ ኃላፊነቶችን በመወጣት ህዝባዊ አጋርነቱን እያረጋገጠ ይገኛል። በዚህም በሰሜኑ የሀገራችን ክፍል በተከሰተው ግጭት የህይወት መስዋዕትነት እየከፈሉ ላሉ የሀገር መከላከያ ሰራዊት፤ የክልሎች ልዩ ሀይሎች፤ ሚሊሻ አባላት እና በጦርነቱ ለተጎዱ ወገኖች ባንኩ 800 ሚሊዮን ብር ድጋፍ ለማድረግ መወሰኑን አቶ አቤ ሳኖ ገልፀው ከዚህ ውስጥ 300 ሚሊዮን ብር ባንኩ ድጋፍ ያደረገ ሲሆን 500 ሚሊዮን ብር ደግሞ የባንኩ ማኔጅመንት እና ስራተኞች የአንድ ወር ደሞዛቸውን ለመለገስ ወስነዋል። ከዚህም በተጨማሪ ዘመቻውን ግንባር ድረስ ሄደው ለመቀላቀል ለሚወስኑ የባንኩ ሰራተኞች ሙሉ ደሞዝና ጥቅማጥቅማቸውን በማስጠበቅ እንዲሁም ሌሎች አስፈላጊ ድጋፎችን ለሠራተኞችና ቤተሰቦቻቸው ለማድረግ ውሳኔ መተላለፉንም አቶ አቤ ይፋ አድርገዋል። አቶ አቤ ሳኖ እንደ ሀገር የባንኩ ስራ አመራርና ሰራተኞች በራሳቸው ፈቃድ ለሀገሩ ውድ ህይወቱን እየሰጠ ለሚገኘው ኃይል ላደረጉት ድጋፍ በባንኩ ስም የላቀ ምስጋናቸውን አቀርበዋል።