ይህ የተገለፀው በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የስያሜ ስፓንስርነት እና በታሜሶል ኮሚዩኒኬሽን አዘጋጅነት ከነሐሴ 15 እስከ ጳጉሜ 5 ቀን 2016 ዓ.ም የሚቆየው ሲቢኢ ብር ፕላስ ኤክስፖ 2017 በኤግዚቢሽን ማዕከል በይፋ በተከፈተበት መርሐግብር ላይ ነው፡፡ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፕሬዚዳንት አቶ አቤ ሳኖ እንዳሉት በፋይናንሱ ዘርፍ ቀዳሚ የሆነው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዘመን አመጣሽ ዲጅታል የባንክ አገልግሎቶችን በመጠቀም ሀገራዊ የግብይት ባህልን እየለወጠ ነው። እንደ አቶ አቤ ገለፃ በአሁኑ ወቅት በባንኩ ከሚከናወነው የገንዘብ ዝውውር ውስጥ 78 በመቶ የሚጠጋው በዲጅታል አማራጮች የሚከናወን ነው። ኤክስፖው ስያሜውን ያገኘበት የሲቢኢ ብር ፕላስ መተግበሪያ ለአጠቃቅም ይበልጥ ምቹና የተለያዩ አማራጮችን የያዘ መሆኑን የገለፁት አቶ አቤ፣ ሕብረተሰቡ ይህንኑ አገልግሎት እንዲጠቀም አበረታተዋል ። እስከ ጳጉሜ 5 ለመጪዎቹ 20 ቀናት በሚቆየው እና ከ500 ሺ በላይ ታዳሚዎች እንደሚጎበኙት በሚጠበቀው ሲቢኢ ብር ፕላስ ኤክስፖ 2017 የአዲስ ዓመት ዋዜማ ኤግዚቢሽን እና ባዛር የመግቢያ ትኬታቸውን በሲቢኢ ብር ፕላስ ለሚቆርጡ ደንበኞች 2.5 ሚሊዮን ብር የምታወጣ የኤሌክትሪክ መኪናን ጨምሮ በየቀኑ የሚወጡ የተለያዩ የገንዘብ ሽልማቶች እንደሚኖሩ ለማወቅ ተችሏል ። ታላቁ የሲቢኢ ብር ፕላስ ኤክስፖ 2017 የአዲስ ዓመት ዋዜማ ኤግዚቢሽን እና ባዛር በይፋ ተከፍቷል፡፡