የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ኬኒያ ፖሊስ ቡሌትስን 1 ለ 0 በማሸነፍ የካፍ ሴቶች ሻምፒዮንስ ሊግ የሴካፋ ሀገራት ሻምፒዮን ሆኗል!
በኢትዮጵያ አስተናጋጅነት ከነሐሴ 11 ቀን 2016 ጀምሮ ሲካሄድ በቆየው በዚህ ሻምፒዮና የኢትዮጵያ ተወካዩ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ማሸነፉን ተከትሎ የሴካፋ ዞንን በመወከል በካፍ የአፍሪካ ሴቶች ሻምፒዮንስ ሊግ የሚሳተፍ ይሆናል፡፡ ዛሬ ከቀኑ 8፡00 ጀምሮ በአበበ ቢቂላ ስታዲየም በተካሄደ የፍፃሜ ጨዋታ ሴናፍ ዋቁማ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክን የምሸነፊያ ግብ ከመረብ አሳርፋለች፡፡ ሴናፍ ዋቁማ በበስድስት ጎሎች የሻምፒዮኑ ከፍተኛ ጎል አስቆጣሪ ሆናለች፡፡ ቀደም ብሎ ከቀኑ 5፡00 ሰዓት በተካሂደ የደረጃ ጨዋታ የዩጋንዳው ካዌምፔ ሙስሊም ሌዲስ የታንዛኒያውን ሲምባ ኩዊንስን 2 ለ 0 በሆነ ውጤት በማሸነፍ ውድድሩን በሦስተኛነት አጠናቋል። የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሴቶች እግር ኳስ ቡድን በ2013 ኬኒያ ባስተናገደችው የመጀመሪያው ውድድር 2ኛ፣ በ2014ቱ የታንዛኒያ ውድድር 3ኛ እንዲሁም በ2015 ዩጋንዳ ላይ ተደርጎ በነበረው ውድድር 2ኛ ደረጃን በመያዝ ማጠናቀቁ ይታወሳል፡፡ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ለመላ የኢትዮጵያ ህዝብ በድጋሚ እንኳን ደስ አላችሁ ይላል!