“ኢትዮጵያን እናልብስ” በሚል መሪ ቃል ዘንድሮ ለሶስተኛ ጊዜ በሚካሄደውና በክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ አነሳሽነት በተጀመረው የአረንጓዴ አሻራ መርሀ-ግብር የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላት፣ ማኔጅመንትና ሠራተኞች በሀገር አቀፍ ደረጃ ከ620 ሺህ በላይ ችግኞችን ተክለዋል። በአዲስ አበባ ከተማ በአይ.ሲ.ቲ ፓርክ ጊቢ ውስጥ በተካሄደው የችግኝ ተከላ መርሀ-ግብር ላይ የተገኙት የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፕሬዚዳንት አቶ አቤ ሳኖ ባደረጉት ንግግር ባንኩ በደን ልማትና በአካባቢ ጥበቃ ዙሪያ ላለፉት አመታት በርካታ ሥራዎችን ማከናወኑን ገልጸው፣ ዘንድሮም ለሶስተኛ ጊዜ በሚካሄደው የአረንጓዴ አሻራ መርሀ-ግብር ላይ መሳተፉን ተናግረዋል፡፡

“ኢትዮጵያን እናልብስ” በሚል መሪ ቃል ዘንድሮ ለሶስተኛ ጊዜ በሚካሄደውና በክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ አነሳሽነት በተጀመረው የአረንጓዴ አሻራ መርሀ-ግብር የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላት፣ ማኔጅመንትና ሠራተኞች በሀገር አቀፍ ደረጃ ከ620 ሺህ በላይ ችግኞችን ተክለዋል። በአዲስ አበባ ከተማ በአይ.ሲ.ቲ ፓርክ ጊቢ ውስጥ በተካሄደው የችግኝ ተከላ መርሀ-ግብር ላይ የተገኙት የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፕሬዚዳንት አቶ አቤ ሳኖ ባደረጉት ንግግር ባንኩ በደን ልማትና በአካባቢ ጥበቃ ዙሪያ ላለፉት አመታት በርካታ ሥራዎችን ማከናወኑን ገልጸው፣ ዘንድሮም ለሶስተኛ ጊዜ በሚካሄደው የአረንጓዴ አሻራ መርሀ-ግብር ላይ መሳተፉን ተናግረዋል፡፡ “የአረንጓዴ አሻራ መርሃ-ግብር የታለመለተን ዓላማ እንዲያሳካ ችግኝ ከመትከል ባለፈ የሚጠበቅብንን ሁሉ ለማድረግ ዝግጁ ልንሆን ይገባል” ያሉት አቶ አቤ ለዚህም የባንኩ ማኔጅመንት ሙሉ ድጋፍ እንደሚያደርግ አረጋግጠዋል፡፡ አቶ አቤ እስካሁን የተተከሉትን ችግኞች በመንከባከብ መጽደቃቸውን መከታተል ዋነኛ ተግባር ሊሆን እንደሚገባም ጠቁመዋል፡፡ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የጤና አገልግሎቶች ዳይሬክተር ሲስተር ፋንቱ ሙሉጌታ በመርሀ-ግብሩ ላይ በመገኘት የባንኩ ሠራተኞች ችግኞችን በሚተክሉበት ወቅት የኮቪድ-19 መከላከያ የጥንቃቄ መርሆዎችን እንዲተገብሩ አሳስበዋል፡፡ “ደን ህይወት ነው” በማለት የተናገሩት ደግሞ የቅርስ ባላደራ ማህበርን በመወከል በመርሀ-ግብሩ ላይ የተገኙት አቶ አህመድ እንድሪስ ናቸው፡፡ አቶ አህመድ ደን ተዘርዝሮ የማያልቅ ጥቅም እንዳለው አውስተው፣ ሁሉም ችግኝ እንዲተክል መልእክታቸውን በማስተላለፍ ስለ ችግኝ አተካከል በመርሀ-ግብሩ ላይ ለተሳተፉት የባንኩ ሠራተኞች አስረድተዋል፡፡ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በሶስቱ የአረንጓዴ አሻራ መርሀ-ግብሮች ላይ በመሳተፍ ከ2 ሚሊዮን በላይ ችግኞችን መትከሉ ታውቋል፡፡