በውጭ ሀገር የምትኖሩ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን የምታደርጉት ድጋፍ ከ 4.4 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር በላይ ደርሷል። ለዚህም አርያነት ላለው ተግባር የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ምስጋናውን አቅርቧል። ====================================== በውጭ ሀገር የምትኖሩ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ለአገር አንድነት፥ ሰላምና ሉአላዊነት ለማስጠበቅ በዲፕሎመሲው እረገድ ትልቅ አቅም ከመፍጠር በላይ በገንዘብ የምታደርጉት ድጋፍ በ “አይዞን ኢትዮጵያ” (eyezonethiopia.com) ብቻ ከ 4.4 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር በላይ ደርሷል። የኢትዮጵያ ንግደ ባንክም በዚህ ገንዘብ መላኪያ ፕላትፎርም የሚላኩ ገንዘቦች የአገልግሎት ክፍያውን በመሸፈን የሚላከው ገንዘብ ሙሉ በሙሉ ለታሰበለት አላማ እንዲውል የበኩሉን ድርሻ እየተወጣ ይገኛል። ይህ የድጋፍ እንቅስቃሴ እንዲሳካ የድርሻችሁን እየተወጣችሁ ላላችሁ ድርጅቶችና ግለሰቦች እንዲሁም ይህንን አስተማማኝ ገንዘብ መላኪያ መተግበሪያ ሰርቶ ተግባር ላይ ላዋለው “ቻፓ የፋይናንስ ቴክኖሎጂ” የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የከበረ ምስጋናውን ያቀርባል። https://combanketh.et/cbeapi/uploads/Notice_08eab14903.pdf #eyezoneethiopia #diaspora #Ethiopia

#