በሲዳማ ክልል የቡና ሃብት ዙሪያ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክና የሚመለከታቸው አካላት ዉይይት አካሄዱ።
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፣ በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት እርሻና ተፈጥሮ ሀብት ልማት ቢሮ እንዲሁም የክልሉ የቡና አቅራቢ እና ላኪዎች በክልሉ የቡና አቅም ፣እድሎች አቅርቦትና ግብይት ዙሪያ በሃዋሳ ከተማ የውይይት መድረክ አካሂደዋል። የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ደቡብ ምእራብ ሪጅን ም/ፕሬዚዳንት አቶ ሙሉነህ ለማ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ባንክ ለዘርፉ በሚሰጠው ብድር እና አመላለስ ዙሪያ መሻሻል የሚገባቸውን ጉዳዮች ለማሻሻል ከባለድርሻ አካላት ጋር እየሰራ መሆኑን ተናግረዋል። አቶ ሙሉነህ የቡና ንግድ ለአገር የሚያስገኘውን የውጪ ምንዛሬ ገቢ ለማሳደግ ሁሉም ባለድርሻ አካላት የሚጠበቅባቸውን ሊወጡ ይገባል ብለዋል። በውይይት መድረኩ በሲዳማ ክልል የቡና አቅም፣ እድሎች አቅርቦትና ግብይት ላይ ያጋጠሙ ችግሮች ላይ በዋናነትም የፋይናንስ አቅርቦት ተግዳሮቶችና ቀጣይ አቅጣጫዎች ላይ ሰነድ ቀረቦ ውይይት ተደርጎበታል። **bold text**