ክቡራን ደንበኞቻች፡ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በቅርቡ በሚሰጣቸው አገልግሎቶች ላይ የክፍያ ማስተካከያ ማድረጉ ይታወቃል። የተሻሻለውን የአገልግሎት ክፍያ በተመለከት ከደንበኞቻችን ባገኘነው ግብረ መልስ መሠረት በአንዳንድ አገልግሎቶች ላይ ድጋሚ የክፍያ ማሻሻያዎች አድርገናል፡፡ በድጋሚ ማሻሻያ የተደረገባቸው አገልግሎቶች እና የተሻሻለው ክፍያ እንደሚከተለው ቀርቧል፡ 1. በወዲአህ በተከፈቱ ሂሳቦች በቅርንጫፍም ሆነ በሞባይል ባንኪንግ የሚደረግ ከሂሳብ ወደ ሂሳብ ገንዘብ የማስተላለፍ አግልግሎት ከክፍያ ነፃ ነው፤ 2. በሙዳራባህ ውል የተከፈቱና እና ለረጅም ጊዜ ያልተንቀሳቀሱ ሂሳቦች (Inactive Accounts) ከክፍያ ነፃ ናቸው፤ 3. በቅርንጫፍ የሚከናወን ከሂሳብ ወደ ሂሳብ ገንዘብ የማስተላለፍ አገልግሎት ክፍያ እንደሚከተለው ተሻሽሏል፡ • ከብር 1 እስከ 10,000 - ብር 5 • ከብር 10,000 እስከ ብር 100,000 - ብር 10 • ከብር 100,001 በላይ - ብር 10 ሲደመር በእያንዳንዱ 100 ሺ 5 ብር (ከ100 ብር ያልበለጠ) 4. በሞባይል ባንኪንግ አገልግሎት የሚከናወን ከሂሳብ ወደ ሌላ ደንበኛ ሂሳብ ገንዘብ የማስተላለፍ አገልግሎት ክፍያ እንደሚከተለው ተሻሽሏል፡ • ከብር 1 እስከ 50,000 - ነፃ • ከብር 50,001 እስከ ብር 100,000 - ብር 5 • ከብር 100,001 እስከ ብር 200,000 - ብር 10 • ከብር 200,001 እስከ ብር 300,000 - ብር 15 • ከብር 300,001 በላይ - ብር 20 5. በሞባይል ባንኪንግ አገልግሎት ሌላ ባንክ ወደሚገኝ ሂሳብ ገንዘብ ለማስተላለፍ (RTGS) ብር 50 የአገልግሎት ክፍያ ያስከፍላል፤ 6. ከ P2P የገንዘብ ዝውውር በ ኢትስዊች (ETSWITCH) 5 ብር እና የኢትስዊች ክፍያን በመደመር የአገልግሎት ክፍያ ይከፈልበታል፤ 7. ወደ ሲቢኢ ብር ሂሳብ ከ50 ብር በታች ለማስገባት የሚከፈል የአገልግሎት ክፍያ የለም፤ 8. በሲቢኢ ብር በቀን ከ3 ጊዜ በላይ የገንዘብ ልውውጥ ሲኖር ገንዘብ የማስገባት አገልግሎት እንደሚከተለው የአገልግሎት ክፍያ ይታሰብበታል፡ • ከብር 50 በታች - ነፃ • ከብር 51 እስከ ብር 500 - ብር 6.45 • ከብር 501 እስከ ብር 2,000 - ብር 7.60 • ከብር 2,001 እስከ ብር 3,000 - ብር 8.18 • ከብር 3,001 እስከ ብር 4,000 - ብር 9.33 • ከብር 4,001 እስከ ብር 5,000 - ብር 10.48 • ከብር 5,001 እስከ ብር 6,000 - ብር 11.63 • ከብር 6,001 በላይ - የሚገባው ገንዘብ 0.2 በመቶ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሁሌም የሚተማመኑበት ባንክ!
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አዲስ መስጠት የጀመራቸው የቁጠባ ሂሳብ አገልግሎቶች 1. እድሜያቸው ከ55 ዓመት በላይ የሆኑ የእድሜ ባለፀጎች የሚከፍቱት ‘ጋሻ የቁጠባ ሂሳብ’ (በሲቢኢ ኑር አገልግሎት ‘ቀዲም ሙዳራባህ የቁጠባ ሂሳብ‘ እና ‘ቀዲም ወዲዓህ የቁጠባ ሂሳብ‘)፣ 2. ደንበኞች ከውጭ ሀገራት የሚላክላቸውን ገንዘብ በባንኩ በመቀበል፣ ወይም በባንኩ የሚመነዝሩትን የውጭ ሀገር ገንዘብ የሚያስቀምጡበት ‘የውጭ ሐዋላ የቁጠባ ሂሳብ‘ ፣ 3. ደንበኞች ለሀገር ውስጥም ሆነ ለውጭ ጉዞ ወጪ መሸፈኛ ገንዘብ የሚቆጥቡበት ‘ሲቢኢ ጉዞ የቁጠባ ሂሳብ‘ (በሲቢኢ ኑር አገልግሎት ‘ሲቢኢ ሪህላ ወዲዓህ የቁጠባ ሂሳብ‘ እና ‘ሲቢኢ ሪሕላ ሙዳራባህ የቁጠባ ሂሳብ‘) ናቸው፡፡ አገልግሎቶቹ ከመደበኛው ቁጠባ ሂሳብ ተጨማሪ ጥቅሞች እንዲኖራቸው ተደርገው የተዘጋጁ ናቸው፡፡ ደንበኞች የቁጠባ ሂሳቦቹን በመክፈት ዘርፈ ብዙ ጥቅሞችን ማግኘት ይችላሉ፡፡