በጀት ዓመቱ አጋማሽ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዲጂታል የክፍያ አማራጮች በተከናወኑ እና በቁጥር ከ910 ሚሊዮን በላይ በሚደርሱ ግብይቶች ከ5.4 ትሪሊዮን ብር በላይ የሚደርስ የገንዘብ እንቅስቃሴ ተከናውኗል፡፡
ባንኩ እስከበጀት ዓመቱ አጋማሽ ከሰጠው የ153.32 ቢሊዮን ብር ብድር ውስጥ 88 በመቶ የሚሆነው ለግሉ ሴክተር የተሰጠ ነው።
በመጀመሪያው ግማሽ ዓመት በሀገር አቀፍ ደረጃ ከተሰበሰበው ተቀማጭ ገንዘብ 58.3 በመቶ መሰብሰብ ችሏል፡፡