News Archive

03 Jul 2025

ባጠናቀቅነው በጀት ዓመት ብቻ ከ515 ቢሊየን ብር በላይ ተጨማሪ አዲስ ተቀማጭ ገንዘብ አሰባስበን አጠቃላይ ተቀማጭ 1.69 ትሪሊዮን ብር በማድረስ ታላቅ ስኬት አስመዝግበናል።

ባጠናቀቅነው የ2024/25 በጀት ዓመት በፈረንጆቹ ጁን ወር መጨረሻ፤ ባንካችን ከ515 ቢሊየን ብር በላይ ተቀማጭ ገንዘብ የማሰባሰብ ተግባር በማሳካቱ የተሰማኝን ከፍ ያለ ደስታ ልገልጽላችሁ እወዳለሁ፡፡ ይህ ለመጀመሪያ ጊዜ በባንካችን የተመዘገበ አዲስ ታሪክ ነው፡፡ ለዚሁ ታላቅ ስኬት አሻራችሁን ላኖራችሁ ሁሉ እንኳን ደሰ አላችሁ እላለሁ፡፡

16 Jun 2025

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የደንበኞች አገልግሎት ወር በተሳካ ሁኔታ እንዲከበር አስተዋፅኦ ላደረጉ አካላት የእውቅናና ምስጋና መርሐ ግብር አካሄደ።

አቶ ኃይለየሱስ የደንበኞች አገልግሎት ወር በተለያዩ ዝግጅቶች መከበሩን አስታውሰው፣ ሁነቱ ባንኩ ከደንበኞቹ ጋር ይበልጥ የተቀራረበበት፣ ለደንበኞች ያለውን ክብር የገለፀበት እና በቀጣይ ሊያሻሽላቸው ስለሚገቡ ጉዳዮችም ግብአት ያገኘበት መሆኑንም ገልፀዋል።

13 May 2025

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አትሌቲክስ ቡድን 54ኛዉ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ዉድድርን በበላይነት አጠናቀቀ፡፡

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አትሌቲክስ ቡድንለሽልማት ከተዘጋጁ ሦስት ዋንጫዎች ሁለቱን ያሸነፈ ሲሆን፣ 12 የወርቅ ፣11 የብር እና 13 የነሀስ ሜዳሊያዎች በማምጣት ከፍተኛ ድል መቀዳጀት ተችሏል፡፡

12 May 2025

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የ2017 የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ ሻምፒዮን!

ቀደም ብሎ ሻምፒዮነቱን ያረጋገጠው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሴቶች እግር ኳስ ቡድን እሁድ ግንቦት 3 ቀን 2017 በሀዋሳ አርቴፊሻል ሜዳ ባካሄደው የመጨረሻ ሳምንት መርሀ ግብር ጨዋታ አዳማ ከተማን 5 ለ 0 በሆነ ሰፊ ውጤት በማሸነፍ በ62 ነጥብ ዋንጫውን አንስቷል።