13 May 2025
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አትሌቲክስ ቡድንለሽልማት ከተዘጋጁ ሦስት ዋንጫዎች ሁለቱን ያሸነፈ ሲሆን፣ 12 የወርቅ ፣11 የብር እና 13 የነሀስ ሜዳሊያዎች በማምጣት ከፍተኛ ድል መቀዳጀት ተችሏል፡፡
12 May 2025
ቀደም ብሎ ሻምፒዮነቱን ያረጋገጠው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሴቶች እግር ኳስ ቡድን እሁድ ግንቦት 3 ቀን 2017 በሀዋሳ አርቴፊሻል ሜዳ ባካሄደው የመጨረሻ ሳምንት መርሀ ግብር ጨዋታ አዳማ ከተማን 5 ለ 0 በሆነ ሰፊ ውጤት በማሸነፍ በ62 ነጥብ ዋንጫውን አንስቷል።
07 May 2025
አቶ አቤ በፓናል ውይይቱ ላይ የውጭ ምንዛሪ አቅርቦት በተለይ ከማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያው ጋር ተያይዞ በከፍተኛ ሁኔታ መሻሻሉን እንዲሁም ከፍተኛ ብድር በተመጣኝ የወለድ ምጣኔ ለረጅም ጊዜ ብድር ከ16.5 ፐርሰንት በማይበልጥ ለማኑፋክቸሪንግ ዘርፉ ባንኩ እያቀረበ እንደሚገኝም ጨምረው ገልጸዋል።
29 Apr 2025
በየቀኑ በርካታ የሳይበር ጥቃቶች ባንኩ ላይ እንደሚሞከሩ የገለፁት አቶ አቤ፣ በባንኩ የተዘረጋው ሲስተም በአግባቡ የሚከላከል እና ሥርዓቱን ሰብሮ ለመግባት የሚፈልግ የትኛውም አጥቂ አልፎ መሔድ የማይችለው መሆኑን ተናግረዋል፡፡