News Archive

14 Jul 2025

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት የተሻለ አፈጻጸም ላስመዘገቡ ሪጅን ፅ/ቤት፣ ዲስትሪክቶች እና ቅርንጫፎች እውቅና እና ሽልማት ሰጠ፡፡

የተቀማጭ ገንዘብ አሰባሰብ፣ የውጭ ምንዛሬ ግኝት እና ኢኮኖሚያዊ አዋጭነት (Economic Profitability) የሥራ አፈፃፀሞች ለሽልማት የተቀመጡ መስፈርቶች ናቸው፡፡

14 Jul 2025

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 14ኛዉ የህብረት ስምምነት የፊርማ ሥነ-ሥርዓት ተካሄደ፡፡

14ኛው የህብረት ስምምነት የባንኩን፣ የማህበሩን እና የሠራተኞችን መብት እና ግዴታ በዝርዝር የያዘ መሆኑን አቶ አበራ ገልፀዋል።

14 Jul 2025

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በሲቢኢ ኑር ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎት የሰበሰበው ተቀማጭ ገንዘብ ከ200 ቢሊዮን ብር በላይ ተሻገረ።

ባለፉት 11 ዓመታት ከ150 ቢሊዮን ብር በላይ በተለያዩ የሥራ ዘርፎች ለተሠማሩ ደንበኞች የፋይናስ አቅርቦት ያደረገ ሲሆን፣ በአሁኑ ጊዜ በዚሁ ዘርፍ ተሰጥቶ የሚገኘው ጠቅላላ የብድር መጠን ከ79.2 ቢሊዮን ብር በላይ ነው።

14 Jul 2025

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በዲጂታል ግብይት የ72 በመቶ ድርሻ እንዳለው ተገለፀ።

እስከ ሜይ 31፣ 2025 በኢንዱስትሪው ከተከናወነው 12 ትሪሊዮን ብር የሚጠጋ ዲጂታል ግብይት 8.6 ትሪሊዮን ብር በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዲጂታል የክፍያ አማራጮች የተከናወነ ሲሆን፣ ይህም ባንኩን 72.2 በመቶ ድርሻ እንዲኖረው አስችሎታል።