14 Jul 2025
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሁሉንም ዜጋ የብድር አገልግሎት ተጠቃሚ ለማድረግ እያደረገ ከሚገኘው ጥረት ጋር በተያያዘ ከ9.1 ቢሊዮን ብር በላይ በዲጂታል አማራጮች ብድር የሰጠ ሲሆን፣ 5.8 ቢሊዮን ብር በቴሌ ብር እንዲሁም 3.3 ቢሊዮን ብር በሲቢኢ ብር አገልግሎት ብድር መሰጠቱን ከቀረበው ሪፖርት ለመረዳት ተችሏል።
14 Jul 2025
በቀረበው የዓመቱ የሥራ አፈፃፀም ሪፖርት ላይ እንደተገለፀው፣ የባንኩ ጠቅላላ ተቀማጭ ገንዘብ 1.69 ትሪሊዮን ብር ደርሷል። ይህም ከአምና ተመሳሳይ ወቅት አፈፃፀም የ43.9 በመቶ እድገት ያለው ነው።
10 Jul 2025
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፕሬዚዳንት አቶ አቤ ሳኖ ዛሬ በተጀመረው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የ2017 (2024/25) በጀት ዓመት ዓመታዊ ጉባኤ ላይ እንደተናገሩት ባንኩ ባለፈው በጀት ዓመት አመርቂ የሥራ አፈፃፀም ያስመዘገበ ሲሆን፣ በታሪኩ ለመጀመሪያ ጊዜም በሁሉም የሥራ አፈፃፀም መለኪያዎች የገበያ ድርሻውን ማሳደግ ችሏል።
10 Jul 2025
የባንኩ የሥራ አመራ ቦርድ አባላት፣ የዋናው መሥሪያ ቤት የሥራ ኃላፊዎች፣ የሪጅን እና የዲስትሪክቶች የሥራ ኃላፊዎች እና ከመላው ሀገሪቱ የመጡ የቅርንጫፍ ሥራ አስኪያጆች በጉባኤው ታድመዋል።