የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ለ#ጽዱኢትዮጵያ ንቅናቄ በእያንዳንዷ 3 ብር መዋጮ ላይ 1 ብር እንደሚያዋጣ አስታወቀ።

በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ይፋ የተደረገው የ“ጽዱ ጎዳና - ኑሮ በጤና” ንቅናቄ በርካቶች በመቀላቀል ድጋፍ እያደረጉ ይገኛሉ። ለ #ጽዱኢትዮጵያ 50 ሚሊየን ብር በአንድ ጀምበር ለማሰባሰብ ሁሉም ዜጋ የሚሳተፍበት የዲጂታል ቴሌቶን በመካሄድ ላይ ይገኛል። በዚህም የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ለ#ጽዱኢትዮጵያ ንቅናቄ በእያንዳንዷ 3 ብር መዋጮ ላይ 1 ብር እንደሚያዋጣ የባንኩ ፕሬዝዳንት አቶ አቤ ሳኖ አስታውቀዋል፡፡ ባንኩ ዛሬ (ግንቦት 4፣ 2016) ለሚካሄደው የዲጂታል ቴሌቶን ሁሉንም የዲጂታል ግብይት መፈጸሚያ አማራጮች በአስተማማኝ ሁኔታ አገልግሎት እንዲሰጡ በማድረግ የበኩሉን አስተዋፅኦ እንዲደሚያደርግ አቶ አቤ ሳኖ በሰጡት ማብራሪያ ገልፀዋል፡፡ አቶ አቤ ለ#ጽዱኢትዮጵያ ንቅናቄ ከዚህ በፊት ካደረጓቸው ድጋፎች በተጨማሪ ለሶስተኛ ጊዜ የ50 ሺህ ብር ድጋፍ አድርገዋል፡፡