የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የውስጥ የእግር ኳስ ውድድር በድምቀት ተከፈተ።

በ12 ቡድኖች መካከል ለአንድ ወር ከአስራ እምስት ቀን የሚካሄደው ይህ ውድድር በአበበ ቢቂላ ስታዲየም እሁድ ግንቦት 25 ቀን 2016 ዓ/ም በይፋ ተጀምሯል ። ውድድሩንም ያስጀመሩት የባንካችን ፕሬዚዳንት አቶ አቤ ሳኖ በመክፈቻ ንግግራቸው እንደነዚህ ዓይነት የውስጥ ውድድሮች የሰራተኞችን ጤና ከመጠበቅ ባሻገር አንድነትን ያጠናክራሉ ብለዋል። በውድድሩ ቦታ የተገኙት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ ኃላፊ አቶ በላይ ደጀን በበኩላቸው እንዲህ አይነት ስፓርታዊ ውድድሮች በሰራተኞች መካከል ያለውን ፍቅር ከማጠናከሩ በላይ ፤ጠንካራ የአካል ብቃት ያለው ሰራተኛ ለመፍጠር እንደሚያስችል ገልጸው ባንኩ ለስፓርቱ ትኩረት በመስጠት እያከናወነ ለሚገኘው እንቅስቃሴ ምስጋና አቅርበዋል።