የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሴቶች እግር ኳስ ቡድን ለፍፃሜ ደርሷል፡፡
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የዩጋንዳውን ካዌምፔ ሙስሊም ሌዲስ 2 ለ 1 በማሸነፍ ለካፍ የሴቶች ሻምፒዮንስ ሊግ የሴካፋ ሀገራት ማጣሪያ ውድድር ፍፃሜ ደርሷል፡፡ መሳይ ተመስገን (45') እና እመቤት አዲሱ (90') የኢትዮጵያ ንግድ ባንክን የማሸነፊያ ግቦች አስቆጥረዋል፡፡ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና የኬኒያው ኬኒያ ፖሊስ ቡሌትስ ሐሙስ ነሀሴ 23 ቀን 2016 ዓ/ም በአበበ በቂላ ስታዲየም በሚደረገው ፍፃሜ ጨዋታ ተፋላሚዎች ናቸው፡፡