የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሥራ ኃላፊዎች ለ “ፅዱ ጎዳና ኑሮ በጤና” መርሀ ግብር የገንዘብ ድጋፍ አደረጉ፡፡

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሥራ ኃላፊዎች ለ “ፅዱ ጎዳና ኑሮ በጤና” መርሀ ግብር የገንዘብ ድጋፍ አደረጉ፡፡ ******************************************** የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፕሬዚዳንት አቶ አቤ ሳኖ ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) በቅርቡ በመዲናችን የመፀዳጃ ቤቶችን ተደራሽ ለማድረግ ላስጀመሩት “ፅዱ ጎዳና ኑሮ በጤና” መርሀ ግብር ብር 50,000 (ሀምሳ ሺ) የገንዘብ ድጋፍ በማድረግ የድጋፍ ማሰባሰብ ዘመቻውን ተቀላቅለዋል፡፡ ሌሎች የባንኩ የሥራ ኃላፊዎችም የአቶ አቤን አርአያነት በመከተል የገንዘብ ድጋፍ ያደረጉ ሲሆን፣ ሁሉም የባንኩ ማህበረሰብ እና ኢትዮጵያውያን ለዚህ መልካም ዓላማ የበኩላቸውን እንዲያበረክቱ አቶ አቤ ጥሪ አቅርበዋል፡፡ የድጋፍ ማሰባሰቢያ ሂሳብ ቁጥር፡ • የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሂሳብ ቁጥር፡ 1000623230248 (Tsidu Ethiopia – Clean Ethiopia) • የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ የውጭ ምንዛሬ ሂሳብ ቁጥር፡ 0101211300016 https://172.31.6.10/cbeapi/uploads/uploads/final_c74872261a.pdf