ባንካችን የአሸናፊነት ዋንጫውን ተረከበ፤

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የወንዶች እግር ኳስ ቡድን የ2016 የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አሸናፊ ሲሆን በ 30 ጨዋታዎች 64 ነጥብ የሰበሰበ ሲሆን በአጠቃላይ 57 ጎሎችን ከመረብ አሳርፏል። ከተቆጠሩት ጎሎች መካከል ግማሽ የሚሆኑት 28 ጎሎች የተቆጠሩት በ3 ተጫዋቾች (አዲስ ግደይ 12፤ ሳይመን ፒተር 9፤ ባሲር ሁመር 7) ነው። ይህም ባማካኝ ወደ ሁለት ጎል የሚጠጋ በያንዳንዱ ጨዋታ በማስቆጠር የሊጉ ድምቀት ነበር። የዋንጫው ባለቤት የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በበርካታ የቡድኑ ደጋፊዎች ፊት ዋንጫውን ተረክቧል። የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዋንጫውን በማንሳቱ ከከፍተኛው ሊግ ወደ ፕሪሚየር ሊግ በተቀላቀለ በመጀመሪያው ዓመት ዋንጫ በማንሳት ከሀዋሳ ከነማ እና ጅማ አባ ጅፋር ቀጥሎ ሶስተኛው ቡድን ሆኖ ተመዝግቧል። በድጋሚ ለመላው የክለባችን ደጋፊዎች በሙሉ እንኳን ደስ አላችሁ!