የተከበሩ አቶ ሞገስ ባልቻ ገብረመድህን ከየካቲት 5 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የዳይሬክተሮች ቦርድ አባል ሆነው እያገለገሉ ይገኛሉ፡፡ በአሁኑ ወቅት በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የዲሞክራሲ ስርዓት ማስተባበርያ ፅ/ቤት ኃላፊ በመሆን እየሰሩ ይገኛሉ፡፡ ቀደም ሲል በጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት በሚኒስትር ማዕረግ የዲሞክራሲ ሥርዓት ማስተባበሪያ ፅ/ቤት ኃላፊ፣ በደቡብ ክልል በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የዲሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ፅ/ቤት ኃላፊ፤ የኢትዮጵያ የገቢዎች ሚኒስቴር ሚኒስትር ሆነው አገልግለዋል፡፡በተጨማሪም በበርካታ የመንግስት የልማት ድርጅቶች የቦርድ አባል በመሆን አገልግለዋል፡፡ በዲቨሎፕመንታል ስተዲስ የማስተርስ ዲግሪ እና በአካውንቲንግ የመጀመሪያ ዲግሪ አላቸው።
Member of the CBE Board Risk Sub-Committee