Avatar of Jonathan Reinink
Member since 2024-02-13

አቶ በረከት ፍስሃፅዮን ከየካቲት 5 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የዳይሬክተሮች ቦርድ አባል በመሆን በማገልገል ላይ ይገኛሉ፡፡ በአሁኑ ወቅት በፕላንና ልማት ሚኒስቴር የልማት ዕቅድ እና የመንግስት ኢንቨስትመንት አስተዳደር ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሆነው እያገለገሉ ነው። በተለያዩ የመንግስት የሥራ ቦታዎች በተሰጣቸው ከፍተኛ የመንግስት ኃላፊነት ሰርተዋል፡፡ በፕላን እና ኢኮኖሚ ሚኒስቴር፣ በአፍሪካ ኢኮኖሚ ኮሚሽን ድጋፍ በመሬት ልማት ማዕቀፍ አማካሪ፣ እንዲሁም በብሔራዊ ፕላን ኮሚሽን የልማት ፕሮጀክቶች ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር በመሆን አገልግለዋል። በክልላዊ እና አካባቢያዊ ልማት ጥናቶች የማስተርስ ዲግሪ እንዲሁም በኢኮኖሚክስ የመጀመሪያ ዲግሪ አግኝተዋል፡፡ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የዳይሬክተሮች ቦርድ ውስጥ የኦዲት ንዑስ ኮሚቴ አባል ናቸው፡፡

Member of the CBE Board Audit Sub-Committee