Avatar of Jonathan Reinink
Member since 2024-11-12

ወይ. ማህሌት ካሳ ከህዳር 3 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የዳይሬክተሮች ቦርድ አባል በመሆን እያገለገሉ ይገኛሉ፡፡ ወ/ሮ ማኅሌት ካሳ በአሁኑ ጊዜ በልደት አበበ ትእዛዙ የሕግ ቢሮ የአቪዬሽን፣የሠራተኛ፣ የኩባንያ አወቃቀር እና ምዝገባ፣ ባንክና ፋይናንስ፣ግብር እና የተፈጥሮ ሀብት ልማት ጉዳዮችን የሚከታተለው የኮርፖሬት እና ንግድ ክፍል ኃላፊ ናቸው፡፡ ከእንግሊዙ ኪንግስተን ዩኒቨርሲቲ በሕግ የሁለተኛ ዲግሪያቸውን በኮርፖሬት እና ፋይናንሺያል ሕግ እንዲሁም ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን በሕግ አግኝተዋል።