Avatar of Jonathan Reinink
Member since 2024-11-12

አምባሳደር ሔኖክ ተፈራ ሻውል ከህዳር 3 ቀን 2017 ዓ/ም ጀምሮ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የዳይሬክተሮች ቦርድ አባል በመሆን እያገለገሉ ይገኛሉ፡፡ በአሁኑ ጊዜ የቦይንግ አፍሪካ ማኔጂንግ ዳይሬክተር ናቸው። አምባሳደር ሄኖክ ተፈራ ሻውል በፈረንሳይ፣ ስፔን፣ ፖርቹጋል፣ ሞናኮ እና ሆሊሲ በአምባሳደርነት፣ እንዲሁም በዩኔስኮ ቋሚ ልዑክ በመሆን ኢትዮጵያን አገልግለዋል፡፡ ከፈረንሳዩ ፓሪስ 1 ፓንተዮን-ሶርቦኔ ዩኒቨርሲቲ (Paris 1 Panthéon-Sorbonne University) በዓለም አቀፍ የኢኮኖሚ ሕግ የሁለተኛ ዲግሪያቸውን ያገኙ ሲሆን፣ ከፈረንሳዩ ኒስ ዩኒቨርሲቲ የሰላምና ልማት የሕግ ተቋም በመንግስታዊ እና በግለሰብ ዓለም አቀፍ ሕግ የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን አግኝተዋል፡፡