አቶ ሔኖክ አሰፋ ከህዳር 3 ቀን 2017 ዓ/ም ጀምሮ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የዳይሬክተሮች ቦርድ አባል በመሆን እያገለገሉ ይገኛሉ፡፡ አቶ ሔኖክ አሰፋ መቀመጫውን አዲስ አበባ ያደረገው ፕሪሳይዝ ዓለማቀፍ አማካሪ ድርጅት መስራች እና አመራር በመሆን እየሠሩ ይገኛል፡፡ አቶ ሔኖክ በኢትዮጵያም ሆነ በውጭ ሀገራት በንግድ ተቋማት በመሥራት እና በማማከር ዘርፍ ከ20 ዓመት በላይ የዘለቀ የሥራ ልምድ አላቸው፡፡ የሁለተኛ ዲግሪያቸውን በኢኮኖሚክስ (ልማት እና ዓለም አቀፍ ንግድ) ፣ እንዲሁም የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን በኢኮኖሚክስ ከአሜሪካው ፎርድሃም ዩኒቨርሲቲ (Fordham University) አግኝተዋል፡፡