በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዋና መሥሪያ ቤት የተፈረመው ይህ ስምምነት 26 የሚሆኑ የፌዴራል የመንግስት መሥሪያ ቤቶች እና በስራቸው የሚገኙ 360 ተቋማት ለተገልገዮች የሚሰጧቸው አገለግሎቶችን ክፍያ በዲጂታል አማራጭ የሚቀበሉበትን መንገድ ያመቻቸ መሆኑ ተገልጿል፡፡
የአል ሃምዱ የሲቢኢ ኑር ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎት ቅርንጫፍም ተመርቆ ሥራ ጀምሯል፡፡
በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሰው ኃይል ልማት ዳይሬክተር ወ/ሮ እየሩሳሌም አመሃ በባንኩ ዋና መሥሪያ ቤት የተካሄደውን የዕውቅና አሰጣጥ መርሃ ግብር በንግግር በከፈቱበት ወቅት እደተናገሩት፣ የተቀናጀ የሥራ ላይ ስልጠና ፕሮግራም የባንኩን የስልጠና አካሄድ በመለወጥ አይነተኛ ሚና አለው፡፡