በፌብሩዋሪ 2025 መጨረሻ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጠቅላላ ተቀማጭ ገንዘብ ብር 1.541 ትሪሊዮን፣ ጠቅላላ የብድርና የቦንድ ክምችት መጠን ብር 1.393 ትሪሊዮን፣ እንዲሁም አጠቃላይ ሃብት ብር 2.073 ትሪሊየን መድረሱን አቶ አቤ በሪፖርታቸው አመላክተዋል፡፡
አቶ አቤ በስምንት ወራት በተቀማጭ ገንዘብ አሰባሰብ የነበረው አፈፃፀም በጁን 2024 ከነበረው ጠቅላላ ተቀማጭ አንጻር የ31.3% ዕድገት እንዲያሳይ ማስቻሉን ገልፀዋል፡፡
በጃኑዋሪ 2025 በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዲጂታል አማራጮች በቁጥር የተከናወነው ግብይት በሀገሪቱ ከተከናወነው ጠቅላላ የዲጂታል ግብይት ከግማሽ በላይ (50.3 በመቶ) እንደነበር አቶ አቤ ገልፀዋል፡፡