የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በሞባይል ባንኪንግ አገልግሎት ያለውን ሰፊ የገበያ ድርሻ በመጠቀም፤ በቨርቹዋል የካርድ አገልግሎት የባንኩን ከ40 ሚሊየን በላይ ደንበኞች የዘመናዊ ዲጂታል የባንክ አገልግሎት ተጠቃሚ ማድረግ እንደሚያስችል ገልፀዋል፡፡
የሲቢኢ ኑር ፕሮዳክት ዴቨሎፕመንት እና ቢዝነስ ኤክስፓንሽን ሥራ አስኪያጅ አቶ አንዋር መሐመድ ደንበኞች ዲጂታል የባንክ አገልግሎቶችን እንዲጠቀሙ ለማበረታታት የሽልማት መርሀ ግብሩ መዘጋጀቱን ገልፀዋል፡፡
ባንኩ በረመዷን ፆም ወቅት ድጋፍ ማድረጉ ለማህበረሰቡ ያለውን ቅርበት እንደሚያሳይም ድጋፍ የተደረገላቸው የህብረተሰብ ክፍሎች ተናግረዋል።