የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ምስጋና አቀረበ፡፡

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፕሬዚዳንት አቶ አቤ ሳኖ ከሲስተም ማሻሻያ ሥራ ጋር በተገናኘ ባንኩ ከሰሞኑ ገጥሞት ከነበረ ችግር ጋር በተያያዘ ለባንኩ ድጋፍ ላደረጉ አካለት በሙሉ ምስጋና አቅርበዋል፡፡ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከተከሰተው ችግር ጋር በተያያዘ እየተከናወኑ ያሉ ተግባራትን ለህብረተሰቡ ለማሳወቅ በዛሬው እለት (መጋቢት 17፣ 2016) ባዘጋጀው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ • የፍትህና የፀጥታ አካላት • የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ፣ • የዩኒቨርሲቲዎች የሥራ ኃላፊዎች እና የተለያዩ የተማሪ አደረጃጀቶች • የመረጃ መረብ ደህንነት አስተዳደር • ኢትዮቴሌኮም • የግል ባንኮች፣ • ማይክሮ ፋይናንስ ተቋማት፣ • የፋይናንስ ደህንነት አገልግሎት • ኢትስዊች፣ • የተለያዩ ፋይናንሻል ቴክኖሎጂ ተቋማት • የፌዴራል እና የክልል ፖሊስ • በየደረጃው ያሉ የመንግስት አስተዳደር መዋቅሮች እና ሌሎች አካላት ችግሩ ከተከሰተበት ጊዜ ጀምሮ ለባንኩ ላደረጉት ድጋፍ እና ትብብር ምስጋና ቀርቦላቸዋል፡፡ የተፈጠረውን ችግር ተረድተው ሥራ በቆመባቸው ሰዓታት በትእግስት በመጠበቅ፣ አላግባብ የተወሰደውን ገንዘብ ለማስመለስ የሚደረገውን ጥረት በማገዝ እና ከባንኩ ጎን በመቆም አብሮነታቸውን እና እምነታቸውን ላሳዩ የባንኩ ደንበኞች ታላቅ ምስጋና ቀርቧል፡፡ ከተፈጠረው ችግር ጋር ተያይዞ ያለውን ትክክለኛ መረጃ ለህብረተሰቡ በተከታታይ ሲያደርሱ ለነበሩ የመገናኛ ብዙሀን ድርጅቶች እንዲሁ ምስጋና ቀርቦላቸዋል፡፡ በመጨረሻም የባንኩ ሠራተኞች በተፈጠረው ችግር ሳይረበሹ እና ሳይደናገጡ የተፈጠረውን ችግር ለመቆጣጠር እና ለማስተካከል ላደረጉት ጥረት ምስጋና ቀርቧል፡፡