የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተጠናቀቀው በጅት ዓመት የተሻለ አፈጻጸም ላስመዘገቡ ዲስትሪክቶች እና ቅርንጫፎች እውቅና እና ሽልማት ሰጠ፡፡

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የ2023/24 በጀት ዓመት የሥራ አፈጻጸም ግምገማ ዓመታዊ ጉባኤ ሐምሌ 13 ቀን 2016 ዓ/ም ሲጠናቀቅ፣ ባለፈው በጀት ዓመት የላቀ አፈጻጸም ላስመዘገቡ ዲስትሪክቶች እና ቅርንጫፎች ዋንጫ፣ የምስክር ወረቀት እና ሽልማት ተበርክቶላቸዋል፡፡ የተቀማጭ ገንዘብ አሰባሰብ፣ የውጭ ምንዛሬ ግኝት እና ኢኮኖሚያዊ አዋጭነት (Economic Profitability) የዲስትሪክቶችን እና ቅርንጫፎችን የሥራ አፈፃፀም ለመመዘን የተቀመጡ መስፈርቶች ናቸው፡፡ ከባንኩ ሰሜን ምስራቅ ሪጅን አጋዚ አቬኑ ቅርንጫፍ (መቀሌ ዲስትሪክት)፣ ፋፂ ቅርንጫፍ (ሽሬ ዲስትሪክት) እና ኩኩፍቶ ቅርንጫፍ (መቀሌ ዲስትሪክት) ከአንድ እስከ ሶስት በመውጣት ተሸልመዋል፡፡ ከደቡብ ምእራብ ሪጅን አዳማ አብይ ቅርንጫፍ (አዳማ ዲስትሪክት) አንደኛ ሲወጣ አዳማ ኢንዱስትሪ ፓርክ ቅርንጫፍ (አዳማ ዲስትሪክት) ደግሞ ሁለተኛ ወጥቷል፡፡ አባላ አባያ ቅርንጫፍ ከወላይታ ሶዶ ዲስትሪክት ሦስተኛ በመውጣት ተሸላሚ ሆኗል፡፡ ከማዕከላዊ ሪጅን ንፋስ ስልክ ቅርንጫፍ አንደኛ በመውጣት ዋንጫውን ሲወስድ፣ ማህተመ ጋንዲ ቅርንጫፍ ሁለተኛ፣ አድዋ ፓርክ ቅርንጫፍ ሦስተኛ በመውጣት ተሸላሚ ሆነዋል፡፡ ከደረጃ 1 ቅርንጫፎች ቦሌ ጃፓን፣ ከደረጃ 2 ቅርንጫፎች አዳማ ኢንዱስትሪ ፓርክ ቅርንጫፍ እንዲሁም ከደረጃ 3 ቅርንጫፎች ባምቢስ ቅርንጫፍ አንደኛ በመውጣት ተሸልመዋል፡፡ ከደረጃ 4 እና ከልዩ ቅርንጫፎች መካከል አዳማ አብይ ቅርንጫፍ አንደኛ በመውጣት የዋንጫ ተሸላሚ ሆኗል፡፡ በኮርፖሬት ደረጃ ንፋስ ስልክ ቅርንጫፍ አንደኛ፣ አዳማ አብይ ቅርንጫፍ ሁለተኛ እንዲሁም ማህተመ ጋንዲ ቅርንጫፍ ሦስተኛ በመሆን ሽልማታቸውን ወስደዋል፡፡ ከዲስትሪክቶች አራዳ ዲስትሪክት አንደኛ በመውጣት የዋንጫ ተሸላሚ ሆኗል፡፡ መቀሌ እና ሽሬ ዲስትሪክት ሁለተኛ እና ሦስተኛ በመውጣት ተሸላሚ ሆነዋል፡፡ ለተሸላሚዎች እንኳን ደስ ያላችሁ እንላለን!