የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በመረጃ ደህንነት ሥርዓት አተገባበር የላቀ አፈጻጸም ላመጡ ዲስትሪክቶች፣ የሥራ ክፍሎች እና ሠራተኞች እውቅና ሰጠ።
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተለያዩ ዝግጅቶች በማክበር ላይ ከሚገኘው የሳይበር ደህንነት ወር ጋር በተያያዘ ጥቅምት 28 ቀን 2017 በባንኩ ዋና መስሪያ ቤት የመሰብሰቢያ አዳራሽ በተዘጋጀ ሥነ-ሥርዓት፣ በመረጃ ደህንነት ሥርዓት አተገባበር የላቀ አፈጻጸም ላመጡ የባንኩ ዲስትሪክቶች፣ የሥራ ክፍሎች እና ሠራተኞች ከባንኩ የሥራ ኃላፊዎች የእውቅና የምስክር ወረቀት ተበርክቶላቸዋል። በዚሁ ሥነ-ሥርዓት ላይ ‘የመረጃ ደህንነትን በመተባበር እናፀናለን’ በሚል ርእሰ ጉዳይ የተካሄደውን የፓናል ውይይት ለመሩ እና ሙያዊ ማብራሪያ ለሰጡ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ሙሁራን እና የዘርፉ ባለሙያዎች ፣የፋይናንስ ተቋማት ተወካዮች፣የመንግሥት ሥራ ኃላፊዎች እንደዚሁ የተሳትፎ የምስክር ወረቀት ተበርክቶላቸዋል፡፡ በመርሀ ግብሩ ላይ የሳይበር ደህንነት ግንዛቤን ለማዳበር የሚረዳ የጥያቄና መልስ ውድድር የተዘጋጀ ሲሆን፣ ከአንደኛ እስከ ሦስተኛ ለወጡ ተሳታፊዎች ሽልማት ተበርክቷል፡፡