በመኾኒ ከተማ ከሲቢኢ ኑር ደንበኞች ጋር የግንዛቤ ማስጨበጫ እና የውይይት መርኃግብር ተካሄደ።

መርኃግብሩ በዋናነት ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎት ዘርፍ ጋር ተያይዞ ከደንበኞች የሚነሱ ፍላጎቶችንና አስተያየቶችን ተቀብሎ አገልግሎቱን የበለጠ ለማሻሻል እና በሲቢኢ ኑር ስለሚሰጡ አገልግሎቶች ግንዛቤ ለማስፋት አላማ ያደረገ ነው፡፡ በዕለቱም የባንካችን የሸሪዓ አማካሪ ኮሚቴ አባል ፕሮፊሰር መሐመድ ሀቢብ፣የሰሜን ምስራቅ ሪጅን የባንክ አገልግሎት መምሪያ ዳይሬክተር አቶ ግሩም ሽመልስ ፣የዋናው መስሪያ ቤት የወለድ ነጻ የባንክ አገልግሎት መምሪያ ዳይሬክተር አቶ አንዋር አብደላ እና የመቐለ ዲስትሪክት ዳይሬክተር አቶ ኤሊያስ ልሳነወርቅ ከመኾኒ ከተማ ደንበኞች ጋር ተወያይተዋል፡፡ ባንኩ ይህንን የውይይት መድረክ በማዘጋጀቱ ደንበኞች ደስታ እንደተሰማቸው በመግለጽ ከባንኩ ጋር ያላቸውን ግንኙነት አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ገልፀዋል፡፡ እንዲሁም ለተነሱ ጥያቄዎችና አስተያየቶች የባንካችን የሸሪዓ አማካሪ ኮሚቴ አባል እና የስራ ሃላፊዎች ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡ ባንካችን እየሰጠ የሚገኘውን ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎት ላይ የሚነሱ ጉድለቶችን በመለየት የደንበኛን ፍላጎት ያከበረ አገልግሎት መስጠት እንዲቻል በዲስትሪክት፣ በሪጅንና በባንክ ደረጃ በፍጥነት እንዲፈቱ አቅጣጫ ተሰጥቷል፡፡