የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሲቢኢ ኑር ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎቱን አስመልክቶ በሠመራ ከተማ የውይይትና የግንዛቤ ማስጨበጫ መርሐ-ግብር አከናወነ።

መርሐ ግብሩ የተካሄደው ስለወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎት ግንዛቤ ለመፍጠርና ከደንበኞች ጋር በሚደረግ ውይይት በሚገኝ ግብረ-መልስ አገልግሎቱን የበለጠ ለማሻሻል እና ለቅሬታዎች ተገቢውን ማስተካከያ ለማድረግ ነው። በዚህም ደንበኞች ባንኩ ትኩረት ሰጥቶ የውይይት መድረክ ማመቻቸቱን በማድነቅ አገልግሎቱን በተመለከተ ማብራሪያ እንዲሰጣቸው ጠይቀዋል። የባንካችን አመራሮችና የሸሪዓ አማካሪዎችም ማብራሪያ ና ገለፃዎችን አድርገዋል ። በተጨማሪም በሠመራ ዲስትሪክት ስር በሚገኙ ቅርንጫፎች እና ደንበኞች ጉብኝት በማካሄድ አገልግሎቱን የበለጠ ለማሻሻል የሚያስችሉ ማስተካከያዎች ተደርገዋል። ባንካችን በሠመራ ዲስትሪክት በ28 ቅርንጫፎች የሲቢኢ ኑር ከወለድ ነጻ የባንክ አገልግሎት እየሠጠ የሚገኝ ሲሆን፣ በዚህም 231 ሺ ቆጣቢዎችን በማፍራት ከ3.9 ቢሊዮን ብር በላይ ገንዘብ አሰባስቧል። በርካታ ደንበኞችንም የሸሪዓ መርህን ያከበረ የፋይናስ አቅርቦት ተጠቃሚ አድርጓል።