ኤግዚቢሽን በደንበኞች የአገልግሎት ወር::

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የደንበኞች አገልግሎት ወር የመክፈቻ መርሃ ግብር ታህሳስ 24 እለት ሲካሄድ የባንካችንን የተለያዩ ስራዎች የሚያስቃኝ ኤግዚቢሽን በባንካችን ዋና መ/ቤት የቢዝነስ ማዕከል ውስጥ ተከፍቷል። የእለቱ የክብር እንግዳ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ የገንዘብ ሚኒስቴርና የባንካችን የቦርድ ሰብሳቢ አቶ አህመድ ሽዴ ከባንካችን ፕሬዚዳንት አቶ አቤ ሳኖ ኤግዚቢሽኑን የከፈቱ ሲሆን በመርሃ ግብሩ ላይ ከተገኙ ደንበኞችና ከባንካችን ከፍተኛ የሥራ ሃላፊዎች ጋር በመሆን ጎብኝተዋል። ኤግዚቢሽኑ በባንካችን የተለያዩ የሥራ ክፍሎች የሚሰሩ ዋና ዋና ሥራዎችን የሚያስቃኝ ሲሆን ለአንድ ሳምንት ለጎብኝዎች ክፍት ሆኖ የሚቆይም ይሆናል።