የደንበኞች የምስጋና እና የውይይት መድረክ በሻሸመኔ ከተማ ተካሄደ፡፡
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከታህሳስ 24 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ እያከበረ ከሚገኘው የደንበኞች አገልግሎት ወር ጋር በተያይዘ በተለያዩ ከተሞች እያካሄደ የሚገኘው የደንበኞች የምስጋና እና የውይይት መድረክ በሻሸመኔ ከተማ ተካሂዷል፡፡ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሲቢኢ ኑር አገልግሎት ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ ኑሪ ሁሴን በውይይት መድረኩ ላይ ተገኝተው ከባንኩ ጋር በታማኝነት እየሠሩ ላሉት ደንበኞች ምስጋና አቅርበዋል፡፡ ባንኩ በቀጣይ ለደንበኞች የተሻለ አገልግሎት ለመስጠት ከውይይት መድረኩ ግብአት እንደሚወስድ አቶ ኑሪ ተናግረዋል፡፡ አቶ ኑሪ ባንኩ ከምንጊዜውም በላይ ብድር እያቀረበ መሆኑን ገልፀው፣ ደንበኞች ቀርበው የአገልግሎቱ ተጠቃሚ ሊሆኑ እንደሚገባ አመልክተዋል፡፡