የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከደንበኞች የሚያገኘው ሀሳብ የባንኩን ራዕይ ለማሳከት የሚደረግውን ጥረት እንደሚያግዝ ተገለፀ፡፡

ይህ የተገለፀው በዛሬው ዕለት የደንበኞች አገልግሎት ወርን ምክንያት በማድረግ በአዳማ ከተማ ከሚገኙ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ደንበኞች ጋር በተደረገው የውይይት መድረክ ላይ ነው፡፡ የባንኩን ደንበኞች ለማመስገን እና ሀሳብ እና አስተያየታቸውን በመስማት ለቀጣይ ሥራ ግባት ለመውሰድ በተዘጋጀው በዚህ መድረክ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሆል ሴል ባንኪንግ ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ ቦኩ ቤኛ፣ የኢንፎርሜሽን ሲስተምስ ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ አማረ አሰፋ እንዲሁም የአዳማ ዲስትሪክት ተጠባባቂ ዳይሬክተር አቶ ድሪባ መኮንን ተገኝተዋል። በውይይቱ የተሳተፉ ደንበኞች የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከጊዜ ወደ ጊዜ ትልቅ ለውጥ እያመጣ መሆኑን ገልፀዋል። በብድር አቅርቦት እና በዲጂታል የባንክ አገልግሎቶች ላይ ትኩረት ተደርጎ ሊሠራ እንደሚገባም ነው የውይይቱ ተሳታፊዎች ያነሱት። በውይይቱ በተነሱ ጉዳዮች ላይ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሆል ሴል ባንኪንግ ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ ቦኩ ቤኛ እና የኢንፎርሜሽን ሲስተምስ ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ አማረ አሰፋ ምላሽ እና ማብራሪያ ሰጥተዋል። በውይይት መድረኩ ለተሳተፉ ደንበኞች የምስጋና እና እውቅና ሰርተፍኬት ተበርክቷል፡፡