የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሴቶች እግር ኳስ ቡድን ለ7ኛ ጊዜ ሻምፒዮን በመሆን ዋንጫውን ተረከበ።
ቀደም ብሎ በ25ኛው መርሀ ግብር ሻምፒዮንነቱን ያረጋገጠው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሴቶች እግር ኳስ ቡድን እሁድ ሐምሌ 7 ቀን 2016 ዓ/ም በአዳማ አበበ ቢቂላ ስታዲየም ባደረገው የሊጉ የመጨረሻ ጨዋታ ይርጋ ጨፌ ቡናን 7 ለ 0 በሆነ ሰፊ ውጤት ማሸነፍ ችሏል። የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጨዋታውን ማሸነፉን ተከትሎ ነጥቡን 65 በማድረስ እና በ66 የጎል ክፍያ በሴቶች ፕሪፒየር ሊግ በተከታታይ ለ4ኛ ጊዜ በአጠቃላይ ለ7ኛ ጊዜ ሻምፒዮን በመሆን ደማቅ ታሪክ መፃፍ ችሏል፡፡ ሴናፍ ዋቁማ (11'፣ 82')፣ ናርዶስ ጌትነት (13')፣ መሳይ ተመስገን (34')፣ አረጋሽ ካልሳ (54’፣ 73') )፣ አርያት ኦዶንጎ (69') የኢትዮጵያ ንግድ ባንክን የማሸነፊያ ጎሎች ያስቆጠሩ ተጫዋቾች ናቸው፡፡ የቡድኑ አጥቂ ሴናፍ ዋቁማ በ28 ጎል ኮኮብ ጎል አስቆጣሪ መሆን ችላለች። የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ለቡድኑ ተጫዋቾች እና አባላት፣ ለደጋፊዎች እና ለመላው የባንኩ ሠራተኞች በድጋሚ እንኳን ደስ አላችሁ ይላል፡፡