የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በጎፋ ዞን ገዜ ጎፋ ወረዳ ኬንቾ ሻቻ ጎዝዲ ቀበሌ በደረሰው የመሬት ናዳ ሳቢያ ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖቻችን የ5 ሚሊዮን ብር ድጋፍ አደረገ፡፡

የባንካችን የሥራ ኃላፊዎች እና ሠራተኞች በግላቸው እያደረጉ ካለው ድጋፍ በተጨማሪ ነው ባንካችን የገንዘብ ድጋፉን ያደረገው፡፡ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በሀገራችን የተለያዩ አካባቢዎች በተፈጥሮም ሆነ በሰው ሠራሽ አደጋዎች ለተጎዱ ወገኖች ፈጥኖ በመድረስ ማኅበራዊ ኃላፊነቱን እየተወጣ የሚገኝ ባንክ መሆኑ ይታወቃል፡፡ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በጤናው ዘርፍ ߹ በትምህርት߹ በአካባቢ ጥበቃ፣ በአረንጓዴ ልማት፣ በሰብአዊ ሥራ ድጋፍ እና በሌሎችም ዘርፎች ማኅበራዊ ኃላፊነቱን ለመወጣት ባለፉት አምስት ዓመታት ከ3 ነጥብ 4 ቢሊዮን ብር በላይ ድጋፍ አድርጓል፡፡