የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አራት አትሌቶችን ለፓሪስ ኦሎምፒክ አስመረጠ።

በአዲስ አበባ ራዲሰን ብሉ ሆቴል በተደረገው የአሸኛኘት መርሐ ግብር የባንኩ የስፖርት ማኅበር ፕሬዚዳት ተወካይና የማዕከላዊ አዲስ አበባ ሪጅን ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ ሚደቅሳ ለአትሌቶቹ መልካም ዕድል በመመኘት የኢትዮጵያን እና የባንኩን ሰንደቅ ዓላማ አበርክተውላቸዋል ። በፓሪስ በሚኖራቸው የውድድር ቆይታም የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሠራተኞችም ሆኑ ባንኩ አስፈላጊውን ድጋፍ ሁሉ እንደሚያደርግላቸው አረጋግጠዋል ። 33ኛው የፓሪስ አሎምፒ ከነገ ሐምሌ 19 ጀምሮ ለ15 ቀናት የሚካሄድ ሲሆን ፍቱይ ተስፋዬ በ10ሺ ሜትር ፣ ብርቄ ኃየሎም በ1500 ሜትር ፣ፅጌ ድጉማ በ800ሜትር ፣ ምስጋናው ዋቂማ በ20 ኪሎ ሜትር እርምጃ ውድድር ሀገራችንን አና የኢትዮጵያ ንግድ ባንክን ወክለው ይወዳደራሉ። ሀገራችን ኢትዮጵያም ይኸው የፓሪስ ኦሎምፒክ 15ኛ የኦሎምፒክ ተሳትፎዋ ሲሆን በሦስት የስፖርት ዓይነቶች አትሌቲክስ፣ ውሀ ዋና እና በቦክስ ትሳተፋለች።