የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሥራ ኃላፊዎችና ሠራተኞች የችግኝ ተከላ መርሐ ግብር አካሄዱ።

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዋናው መ/ቤት፣ አራዳ፣ የካ እና መገናኛ ዲስትሪክት የሥራ ኃላፊዎችና ሠራተኞች በቦሌ ለሚ ኢንዱስትሪ ፖርክ ውስጥ የችግኝ ተከላ መርሐ ግብር አካሂደዋል። ከዋናው መ/ቤት በአካል ብቃት እንቅስቃሴ የተጀመረው መርሐ ግብሩ በቦሌ ለሚ ኢንደስትሪ ፓርክ ውስጥ በድምቀት ከቀጠለ በኋላ የሥራ ኃላፊዎቹና ሠራተኞቹ ችግኝ ተክለዋል። የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፕሬዚዳንት ተወካይ አቶ ኤፍሬም መኩሪያ የኢትዮጵያ ባንክ ባለፉት ዓመታት በገፈርሳ፣ በሰበታ፣ በቢሾፍቱ፣ በጣሊያን ምሽግ፣ በእንጦጦ ተራራ፣ በቦሌ ለሚ ኢንዱስትሪ ፓርክ፣ እንዲሁም በአይሲቲ ፓርክ ችግኝ መትከሉን በማስታወስ ባንኩ የቆየ ልምድ ያዳበረ መሆኑን ተናግረዋል። በዛሬው ዕለትም በድጋሚ በቦሌ ለሚ ኢንደስትሪ ፓርክ ውስጥ ችግኝ መተከሉን በማስታወስ ችግኝ ከመትከል በተጨማሪም ባንኩ በእንክብካቤና ሌሎችም የአካባቢ ጥበቃ ሥራዎች ላይ በመሳተፍ ማኅበራዊ ኃላፊነቱን እየተወጣ መሆኑን አቶ ኤፍሬም አያይዘዉ ገልፀዋል። የችግኝ ተከላ መርሐ ግብሩ በአዲስ አበባ በሚገኙ ሌሎችም ዲስትሪክቶችና ከአዲስ አበባ ውጪ ባሉት ሁሉም ዲስትሪክቶች በቀጣይነት የሚካሄድ መሆኑ ታውቋል።