![](/cbeapi/uploads/photo_2024_08_15_16_32_42_7ee6e992c1.jpg)
ነሐሴ 9 ቀን 2016 ዓ.ም በሃያት ሪጀንሲ ሆቴል በተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ በአዲስ አበባ ኤግዚቢሽን ማዕከል የሚካሄደው የ2017 አዲስ ዓመት ኤክስፖ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በቅርቡ አሻሽሎ ሥራ ላይ ባዋለው ሲቢኢ ብር ፕላስ ተሰይሟል፡፡ በጋዜጣዊ መግለጫው ‘አዲስ ነገር በአዲስ ዓመት ሲቢኢ ብር ፕላስ 2017 ኤክስፖ' ከ 200 በላይ ድርጅቶች አዳዲስ ምርትና አገልግሎቶች ይቀርባሉ። በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የማርኬቲንግ ዳይሬክተር አቶ ዮናስ ኃ/ገብርኤል የኤክስፖው የመግቢያ ትኬቶች ከዛሬ ጀምሮ በሲቢኢ ብር ፕላስ መተግበሪያ ብቻ እንደሚሸጡ ተናግረዋል፡፡ ከመግቢያ ትኬት በተጨማሪ ምርትና አገልግሎቶችን በሲቢኢ ብር ፕላስ መተግበሪያ አማካኝነት መገበያየት እና መሽለም እንደሚቻልም የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሞባይል መኒ ዳይሬክተር አቶ መንግስቱ እንዳላማው ተናግረዋል፡፡ በሲቢኢ ብር ፕላስ መተግበሪያ ተጠቅመው ትኬት ለሚቆርጡ የኤክስፖ ተሳታፊዎች 2.3 ሚሊዮን ብር የሚያወጣ ተሽከርካሪና በየዕለቱ ሌሎች ሽልማቶችን የሚያስገኙ እጣዎች እንደሚኖሩም ተገልጿል፡፡ የሲቢኢ ብር ፕላስ መተግበሪያን ተጠቅመው በመጀመሪያ ሁለት ቀናት ለሚገበያዩ ለ10 ሺህ ሰዎች የነፃ መግቢያ ትኬት መዘጋጀቱም ተገልጿል። መተግበሪያውን በአዲስ መልክ አውርደው ለሚጠቀሙ 200 ሺህ ሰዎች 1ሚሊያን ብር ሽልማት ተዘጋጅቷል ፡፡ በሲቢኢ ብር ፕላስ የተሰየመው ይህ ኤክስፖ በተለያዩ ዓለማት የሚኖሩ ኢትዮጵያን ለወዳጅ ዘመዶቻቻው ‘በ Ethio-Direct’ በኩል ትኬት እና የተለያዩ እቃዎችን መግዛት እንደሚቻል ተገልጿል።