የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ለሲዳማ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የፋይናንስ ቢሮ እውቅና ሰጠ።

በክልሉ በሚኖረው የፋይናንስ ተደራሽነት፣ የኢኮኖሚ እና ኢንቨስትመንት ልማት እንቅስቃሴ ጉልህ አስተዋፅኦ እያደረገ ለሚገኘው ለሲዳማ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የፋይናንስ ቢሮ ባንኩ እውቅና ሰጥቷል። በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሀዋሳ ዲስትሪክት ዳይሬክተር አቶ ወዬሳ ጥላሁን ባንኩ በክልሉ ለሚኖረው ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ አስተዋፅኦ ከቢሮው ጋር ጥብቅ የስራ ግንኙነት ያለው በመሆኑ እውቅና እንደተሰጠው ተናግረዋል። በሲዳማ ብሄራዊ ክልል መንግስት የፋይናንስ ቢሮ ሃላፊ አቶ ይሌ ሀርሲሳ በበኩላቸው ለተቋማቸው ለተደረገው እውቅና አመስግነው ባንኩ በክልሉ ኢኮኖሚና ኢንቨስትመንት ላይ ጉልህ ሚና እያበረከተ መሆኑን ገልፀዋል። ክልሉ ወደፊትም ከባንኩ ጋር በጋራ ለመስራት ዝግጁ መሆኑንም ተናግረዋል።