የፖስ ተጠቃሚ ደንበኞች የሽልማት መርሐ-ግብር እድለኞች ሽልማታቸውን ተረከቡ፡፡

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የገና እና የጥምቀት በዓላትን ምክንያት በማድረግ ለፖስ ተጠቃሚዎች ባዘጋጀው የሽልማት መርሐ ግብር ተሳትፈው ዕጣ የወጣላቸው እድለኞች በባንኩ ዋና መሥሪያ ቤት በመገኘት ሽልማታቸውን እየተረከቡ ነው፡፡ እስከ ጥር 27 ቀን 2017 ዓ.ም በሚቆየው በዚህ የሽልማት መርሀ ግብር በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፖስ ከ1 ሺ ብር ጀምሮ የሚገበያዩ 315 ደንበኞች በተከታታይ በሚወጡ ዕጣዎች ተሸላሚ ይሆናሉ፡፡