የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ለንብ ኢንተርናሽናል ባንክ 25ኛ አመት የ''እንኳን ደስ አላችሁ'' መልዕክት አስተላለፈ።

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ልዑካን ቡድን በንብ ኢንተርናሽናል ባንክ ዋና መስሪያ ቤት በመገኘት ከባንኩ ፕሬዝዳንት አቶ አቤ ሳኖ የተላከውን ''የእንኳን ደስ አላችሁ'' መልዕክት እና ስጦታ ለባንኩ ዋና ሥራ አስፈፃሚና ሌሎችም የሥራ ሃላፊዎች አበርክቷል። ልዑካኑን የመሩት የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የኮርፖሬት ኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ አልሰን አሰፋ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እንደ ንብ ባንክ ያሉ ትላልቅ ተቋማትን ለምስረታ በዓላቸው የ''እንኳን አደረሳችሁ'' መልካም ምኞት በማስተላለፍ በዘርፉ ያለውን አዎንታዊ ስሜት ለማሳደግ እየሰራ መሆኑን ተናግረዋል። ንብ ባንክ ባሳለፋቸው 25 ዓመታት ለተቀዳጀው ስኬት የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ትልቅ ቦታ እንደሚሰጠውም ነው አቶ አልሰን የተናገሩት። የንብ ኢንተርናሽናል ባንክ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ሄኖክ ከበደ በበኩላቸው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የጀመረው ተግባር በአርአያነት የሚነሳና በዘርፉ ያልተለመደ እንዲሁም በንብ ባንክም የመጀመሪያው በመሆኑ የመልካምነት ስሜትን የሚያጎለብት ነው፤ ለዚህም እናመሰግናለን ብለዋል። ሁለቱ ተቋማት ወደፊትም በተለያዩ የሥራ ምዕራፎች ትብብራቸውን አጠናክረው እንዲቀጥሉ ለማድረግም መሰል እንቅስቃሴዎች ሚናቸው ላቅ ያለ መሆኑን ዋና ሥራ አስፈፃሚው ተናግረዋል። የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሁሌም የሚተማመኑበት ባንክ!