News Archive

31 Oct 2024

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሥራ ኃላፊዎች በ2017 በጀት ዓመት የመጀመሪያ 100 ቀናት ሀገራዊ የሪፎርም እና ዋና ዋና የኢኮኖሚ አፈፃፀም ላይ ውይይት አደረጉ፡፡ • የባንኩ የመጀመሪያ ሩብ ዓመት የሥራ አፈፃፀምም በዋና ዋና መለኪያዎች ተዳሷል፡፡

ኢትዮጵያ የተሟላ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ተግባራዊ ባደረገችበት የ2017 በጀት ዓመት የመጀመሪያ 100 ቀናት በነበረው ሀገራዊ አፈፃፀም ላይ የተዘጋጀ ሪፖርት ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል፡፡

28 Oct 2024

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከብሔራዊ ተሃድሶ ኮሚሽን እና ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት የልማት ፕሮግራም (UNDP) ጋር በጋራ ለመስራት የሚያስችለውን የሶስትዮሽ የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረመ።

የስምምነቱ ዋና አላማ በትግራይ ክልል በጦርነት ወቅት የተሳተፉ ተዋጊዎችን ትጥቅ የማስፈታትና መልሶ ለማቋቋም የሚውለውን የገንዘብ ዝውውር ለማቀላጠፍ ነው።

28 Oct 2024

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና ሀይብሪድ ዲዛይን ኅ.የተ.የግ.ማ (ራይድ ትራንስፖርት) በተለያዩ ዘርፎች በጋራ መሥራት የሚያስችላቸውን ስምምነት ተፈራረሙ፡፡

የራይድ ትራንስፖርት ተጠቃሚ ደንበኞችን በባንኩ ዲጂታል የክፍያ አማራጮች ክፍያቸውን መፈፀም ለማስቻል፣ ራይድ በሚያቀርባቸው የተለያዩ ዲጂታል ፕላትፎርሞች ላይ በሀገር ውስጥም ሆነ ከሀገር ውጭ በጋራ ለመሥራት፣ ለኤሌክትሪክ መኪኖች ግዥ የፋይናንስ አገልግሎት ለማቅረብ እንዲሁም በቀጣይ በሌሎች ጉዳዮች ላይ በጋራ ለመሥራት የሚያስችል ስምምነት ነው፡፡

14 Oct 2024

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በግብር ከፋዮች ሽልማት የፕላቲኒየም ደረጃና ልዩ ተሸላሚ ሆነ፡፡

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሽልማት መርሐ ግብሩ ከተጀመረበት ጊዜ አንስቶ የፕላቲኒየም ደረጃ ተሸላሚ ሆኖ የቆየ ሲሆን በዚህኛው ዙር ከፕላቲኒየም በተጨማሪ ልዩ ተሸላሚም ሆኗል፡፡