News Archive

09 Nov 2024

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ‘የመረጃ ደህንነትን በመተባበር እናፀናለን’ በሚል ርእሰ ጉዳይ የፓናል ውይይት አካሄደ።

የፓናል ውይይቱን በንግግር የከፈቱት የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፕሬዚዳንት አቶ አቤ ሳኖ የሳይበር ደህንነት ጉዳይ ከመቼውም ጊዜ በላይ ትኩረት የሚያስፍልገው እንደሆነ ገልፀው፣ ባንኩ ከባለድርሻ አካላት ጋር በጋራ ለመስራት የሚያስችለውን ለመምከር የውይይት መድረኩን ማዘጋጀቱን ገልፀዋል።

09 Nov 2024

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክን ካፒታል ከፍ የሚያደርግ ረቂቅ አዋጅ አፀደቀ::

የልማት ድርጅቶች ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የወሰዱትን ብድር ባለመመለሳቸውና የብድር ወለዱም በጣም ከፍ በማለቱ በባንኩ ላይ ጫና መፍጠሩን አብራርተው፤ ባንኩ የሀገሪቱ ዋነኛ ተቋም በመሆኑ 900 ቢሊየን ብሩ የመንግስት ዕዳ ሰነድ ሆኖ እንዲከፈል እና መነሻ ካፒታሉም ከፍ እንዲል ውሳኔ ላይ መድረሱን አስረድተዋል፡፡

07 Nov 2024

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ደስታውን ገለፀ፡፡

የባንኩን ፕሬዚዳንት የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት የኮርፖሬት ኮሙኒኬሽን ዳይሬክተሩ አቶ አልሠን አሰፋ ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚ አስረክበዋል፡፡

07 Nov 2024

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ለሲዳማ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የፋይናንስ ቢሮ እውቅና ሰጠ።

በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሀዋሳ ዲስትሪክት ዳይሬክተር አቶ ወዬሳ ጥላሁን ባንኩ በክልሉ ለሚኖረው ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ አስተዋፅኦ ከቢሮው ጋር ጥብቅ የስራ ግንኙነት ያለው በመሆኑ እውቅና እንደተሰጠው ተናግረዋል።