News Archive

13 Dec 2024

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሲቢኢ ኑር ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎቱን አስመልክቶ በሠመራ ከተማ የውይይትና የግንዛቤ ማስጨበጫ መርሐ-ግብር አከናወነ።

የአል ሃምዱ የሲቢኢ ኑር ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎት ቅርንጫፍም ተመርቆ ሥራ ጀምሯል፡፡

13 Dec 2024

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተቀናጀ የሥራ ላይ ሥልጠና ለተሳተፉ የቦሌና ቂርቆስ ዲስትሪክት ሠራተኞች ዕውቅና ሰጠ፡፡

በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሰው ኃይል ልማት ዳይሬክተር ወ/ሮ እየሩሳሌም አመሃ በባንኩ ዋና መሥሪያ ቤት የተካሄደውን የዕውቅና አሰጣጥ መርሃ ግብር በንግግር በከፈቱበት ወቅት እደተናገሩት፣ የተቀናጀ የሥራ ላይ ስልጠና ፕሮግራም የባንኩን የስልጠና አካሄድ በመለወጥ አይነተኛ ሚና አለው፡፡

29 Nov 2024

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከኢትዮጵያ ግሬት ራን ጋር በመተባበር በእንጦጦ ፓርክ የሚደረገውን ወርሃዊ የሩጫ ውድድርን (ENTOTO PARK CBE RUN) ስፖንሰር አደረገ፡፡ • የመሮጫ ትኬቱ በሲቢኢ ብር ይቆረጣል።

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ተጠባባቂ ፕሬዚዳንት አቶ ደረጄ ፉፋ እንደተናገሩት፣ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ማህበራዊ ኃላፊነቱን ከሚወጣባቸው መንገዶች አንዱ የስፖርቱን ዘርፍ መደገፍ ነው፡፡

29 Nov 2024

ሲቢኢ ኑር ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎት ዓለም አቀፍ ሽልማት አገኘ!

እንኳን ደስ አለን! ሲቢኢ ኑር ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎት ዓለም አቀፍ ሽልማት አገኘ! የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በ2024 በኢትዮጵያ ከወለድ ነፃ የሪቴይል የባንክ አገልግሎት አሰጣጥ ጥራት የላቀ አፈፃፀም በማስመዝገብ በ ‘’Best Islamic Retail Banking Widow for Service Quality and Operations in Ethiopia 2024’’ ዘርፍ ካምብሪጅኢፋ /CAMBRIDGEIFA/ በተሰኘው ዓለም አቀፍ የሽልማት ድርጅት ተሸላሚ ሆኗል፡፡