News Archive

05 Aug 2024

ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ መስኮች በጋራ መስራት የሚያስችላቸውን የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረሙ፡፡

ስምምነቱ ሁለቱ ተቋማት በጥናት እና ምርምር መስክ፣ በሰው ኃይል ልማት፣በቴክኖሎጂ እና ዲጂታል ዘርፍ እንዲሁም የባንክና ፋይናንስ ዘርፉን በሚያግዙ የፈጠራ ሥራዎች ላይ በጋራ ለመሥራት ያስችላቸዋል፡፡

29 Jul 2024

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ለግሉ ክፍለ ኢኮኖሚ ያቀረበው ብድር የንግድ እንቅስቃሴውን ማሳለጡ ተገለፀ፡፡

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የፓሪስ 2024 ኦሎምፒክ ቀጥታ የቴሌቪዥን ስርጭት ልዩ የፕላቲኒየም ደረጃ ስፖንሰር ነው፡፡

27 Jul 2024

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አራት አትሌቶችን ለፓሪስ ኦሎምፒክ አስመረጠ።

በፈረንሳይ ሀገር በፓሪስ ከተማ 33ኛው የአሎምፒክ ውድድር ከ ሐምሌ 19 ቀን 2016 ዓ/ም ጀምሮ ለ15 ቀናት ይካሄዳል፡፡ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክም አራት አትሌቶችን በአትሌቲክስ እንዲወዳደሩ ማስመረጥ ችሏል፡፡ ለአትሌቶቹም የኢትዮጵያን እና የባንኩን ሰንደቅ ዓላማ በማበርከት የመልካም ምኞት አሸኛኘት አድርጎላቸዋል፡፡

27 Jul 2024

የሲቢኢ ብር ተጠቃሚዎች ቁጥር ከ11.7 ሚሊዮን በላይ ደረሰ፡፡

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በሰኔ 2009 ዓ.ም የሲቢኢ ብር አገልግሎትን እንደ አንድ የዲጂታል የባንክ አገልግሎት አማራጭ አድርጎ ጀምሯል፡፡ ባንኩ የሲቢኢ ብር አገልግሎቱን ለማሻሻል በየጊዜው በወሰዳችው እርምጃዎች በሞባይል መኒ አገልግሎት ያለውን የገበያ ድርሻ አጠናክሮ ለመቀጠል አስችሎታል፡፡ ሲቢኢ ብር ፕላስ (CBEBirr Plus) በሚል በአዲስ መልክ አሻሽሎ ያቀረበውን የሲቢኢ ብር መተግበሪያ በሐምሌ 18 ቀን 2016 ዓ.ም በባንኩ ዋና መሥሪያ ቤት የመሰብሰቢያ ማዕከል በይፋ ሥራ ሲያስጀምር የሲቢኢ ብር ተጠቃሚዎች ቁጥር ከ11.7 ሚሊዮን በላይ አድርሶ ነው፡፡