25 Jul 2024
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በጤናው ዘርፍ ߹ በትምህርት߹ በአካባቢ ጥበቃ፣ በአረንጓዴ ልማት፣ በሰብአዊ ሥራ ድጋፍ እና በሌሎችም ዘርፎች ማኅበራዊ ኃላፊነቱን ለመወጣት ባለፉት አምስት ዓመታት ከ3 ነጥብ 4 ቢሊዮን ብር በላይ ድጋፍ አድርጓል፡፡
24 Jul 2024
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፕሬዚዳንት አቶ አቤ ሳኖ ለባንኩ ትርፋማነትና ስኬታማነት ባሳዩት ብቃት ያለው አመራር የ2016 ዓ.ም. የዳይመንድ ደረጃ ኒሻን እና ዕውቅና ተበርክቶላቸዋል፡፡ በሽልማት ሥነ-ሥርዓቱ ላይ በመገኘት ዕውቅናውንና ሽልማቱን የተረከቡት የባንኩ የሰው ኃይል ም/ፕሬዚዳንት አቶ ኤፍሬም መኩሪያ እና ሌሎችም የባንኩ ኃላፊዎች በፕሬዚዳንቱ ቢሮ በመገኘት ሽልማቱን ለአቶ አቤ ሳኖ አስረክበዋቸዋል፡፡
24 Jul 2024
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፕሬዚደንት አቶ አቤ ሳኖ በፊርማ ሥነ -ሥርዓቱ ላይ እንደተናገሩት ከ14.4 ቢሊየን ብር በላይ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በኩል የሚሸፈን ሲሆን፤ ቀሪው 1.1 ቢሊየን ብር በኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር ይሸፈናል፡፡
24 Jul 2024
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፕሬዚዳንት አቶ አቤ ሳኖ በከፍተኛ አመራሮች ዘርፍ የዳይመንድ ደረጃ ኒሻን ተሸላሚ ሆነዋል፡፡