24 Jul 2024
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከሲስተም ማሻሻያ ሥራ ጋር በተገናኘ መጋቢት 7 ቀን 2016 ዓ.ም. በተፈጠረ ችግር ምክንያት ያለአግባብ ተወስዶ የነበረውን ገንዘብ በማስመለስ ሂደት የላቀ አስተዋፅኦ ላበረከቱ የባንኩ ሠራተኞች፣ ዲስትሪክቶች እና ቅርንጫፎች፣ የመንግስት አካላት እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ምስጋና አቅርበዋል፡፡
24 Jul 2024
የተቀማጭ ገንዘብ አሰባሰብ፣ የውጭ ምንዛሬ ግኝት እና ኢኮኖሚያዊ አዋጭነት (Economic Profitability) የዲስትሪክቶችን እና ቅርንጫፎችን የሥራ አፈፃፀም ለመመዘን የተቀመጡ መስፈርቶች ናቸው፡፡
24 Jul 2024
ከሲስተም ማሻሻያ ሥራ ጋር በተገናኘ መጋቢት 7 ቀን 2016 ዓ.ም. በተፈጠረ ችግር ምክንያት ያለአግባብ ተወስዶ የነበረውን ገንዘብ ለማስመለስ ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይሉ ሌት ቀን በትጋት ሙያዊ ኃላፊነታቸውን የተወጡ ሰባት የባንኩ ሠራተኞች ከባንኩ ፕሬዚዳንት አቶ አቤ ሳኖ እጅ የምስክር ወረቀት እና ሽልማት ተቀበለዋል፡፡
24 Jul 2024
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፕሪዚዳንት አቶ አቤ ሳኖ በጉባኤው ማጠቃለያ መልእክታቸው የባንኩን የቀጣይ ዓመት የትኩረት አቅጣጫዎች አመልክተዋል፡፡