08 Feb 2022
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 80ኛ ዓመት የምሥረታ በዓል እና የዋና መ/ቤት ሕንፃ ምርቃት የካቲት 6 ቀን 2014 ዓ.ም በደማቅ ሥነ ሥርዓት እንደሚከናወን ተገለጸ፡፡ • ይህ የተገለፀው በአዲሱ ዋና መሥሪያ ቤት ህንፃ 48ኛ ፎቅ በተዘጋጀ ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ነው፡፡
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 80ኛ ዓመት የምሥረታ በዓል እና የዋና መ/ቤት ሕንፃ ምርቃት የካቲት 6 ቀን 2014 ዓ.ም በደማቅ ሥነ ሥርዓት እንደሚከናወን ተገለጸ፡፡
• ይህ የተገለፀው በአዲሱ ዋና መሥሪያ ቤት ህንፃ 48ኛ ፎቅ በተዘጋጀ ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ነው፡፡
========
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 80ኛ ዓመት የምስረታ በዓሉን በሚያከብርበት የካቲት 6 ቀን 2014 ዓ.ም አዲሱን የዋና መ/ቤት ህንፃ ምርቃት በደማቅ ሥነ ሥርዓት እንደሚያከናውን አስታውቋል፡፡
ሁነቱን በማስመልከት ጋዜጣዊ መግለጫ የሰጡት የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፕሬዚዳንት አቶ አቤ ሳኖ እንዳሉት ባንኩ ኢትዮጵያንም ሆነ ባንኩን በአፍሪካ በቀዳሚነት ከሚያስነሱ ፕሮጀክቶች አንዱ የሆነውን ሰማይ ጠቀስ ህንፃ በ80ኛ ዓመቱ ላይ እውን አድርጓል፡፡