News Archive

20 Aug 2022

በሲቢኢ ብር መተግበሪያ ‘Market Place’ የዲጂታል ትኬት ሽያጭ አገልግሎት መስጠት ተጀመረ!

ከነሀሴ 14 - ጳጉሜን 5 ቀን 2014 ዓ.ም በአዲስ አበባ ኤግዚቢሽን ማእከል የሚካሄደው የአዲስ አመት ኤግዚቢሽን እና ባዛር ተሳታፊዎች የሲቢኢ ብር መተግበሪያ ‘Market Place’ አገልግሎትን በመጠቀም ባሉበት ቦታ ሆነው የመግቢያ ትኬት መቁረጥ የሚያስችል አገልግሎት መስጠት ተጀመረ።

15 Aug 2022

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጠቅላላ ተቀማጭ ገንዘብ 890.1 ቢሊዮን ብር ደረሰ፡፡

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በ2014 (2021/22) በጀት ዓመት 154.9 ቢሊዮን ብር ተጨማሪ የተቀማጭ ገንዘብ በማሰባሰብ ጠቅላላ የተቀማጭ ገንዘቡን 890.1 ቢሊዮን ብር ማድረሱን የባንኩ ፕሬዚዳንት አቶ አቤ ሳኖ አስታውቀዋል፡፡ ባንኩ በበጀት ዓመቱ 27 ነጥብ 5 ቢሊየን ብር ትርፍ ያገኘ ሲሆን ይህም ከእቅዱ 16.3 በመቶ፣ ካለፈው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር ደግሞ የ43 ነጥብ 9 በመቶ ብልጫ እንደሚያሳይ አቶ አቤ ገልጸዋል።

24 Jun 2022

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ለ10 አመት የሚቆይ የ200 ሚሊዮን ብር የስፖንሰርሺፕ ስምምነት በሸራተን አዲስ ሆቴል ተፈራረሙ፡፡

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ለ10 አመት የሚቆይ የ200 ሚሊዮን ብር የስፖንሰርሺፕ ስምምነት በሸራተን አዲስ ሆቴል ተፈራረሙ፡፡ ========================= ሰኔ 16 ቀን 2014 ዓ.ም በሸራተን አዲስ ሆቴል የተፈረመው ስምምነት የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን የአገልግሎት ጥራትና ተደራሽነቱን ለማሳደግ የጀመረውን የዘመናዊ ስቱዲዮ ግንባታ በአጋርነት ለመሥራት የሚያስችል ነው፡፡

05 Mar 2022

የ “ይቆጥቡ፤ ይሸለሙ!” መርሀ ግብር የህብረተሰቡን የቁጠባ ባህል እንዳበረታታ ተገለፀ፡፡

ይህን የገለፁት የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ለ10ኛ ዙር ያዘጋጀውን “የይቆጥቡ፤ ይሸለሙ!” መርሀ ግብር ዕጣ የካቲት 25 ቀን 2014 ዓ.ም ባወጣበት ስነ-ስርአት ላይ የተገኙት የባንኩ ፕሬዚዳንት አቶ አቤ ሳኖ ናቸው፡፡ የሽልማት መርሀ-ግብሩ በ2004 ዓ.ም መጀመሩን ያስታወሱት አቶ አቤ፣ ለ10 ዙር ሲካሄድ በርካቶችን ቁጠባን ባህላቸው ማድረግ ከማስቻሉም በላይ የትልልቅ ሽልማቶች እድለኛም እንዳደረገ ገልፀዋል፡፡ ባንኩ የ“ይቆጥቡ፤ ይሸለሙ!” መርሀ ግብር በህብረተሰቡ የቁጠባ ባህል ላይ ያመጣውን ተጽእኖ ለመፈተሸ ጥናት ማስጠናቱን አቶ አቤ የገለጹ ሲሆን፣ የጥናቱ ውጤትም በመርሀ-ግብሩ ሳቢያ ብዙ ደንበኞች በመደበኛነት እንዲቆጥቡና ቁጠባቸውንም ለረጅም ጊዜ ሳያወጡ እንዲቆዩ እንዳስቻላቸው ማሳየቱን ተናግረዋል፡፡