News Archive

03 Mar 2023

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ በጋራ ለመስራት የሚያስችላቸውን ስምምነት ተፈራረሙ።

ስምምነቱን የፈረሙት የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፕሬዝዳንት አቶ አቤ ሳኖ እና የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ስራአስኪያጅ አኑዋር ሱሳ ናቸው። የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፕሬዝዳንት አቶ አቤ ሳኖ በስምምነቱ ወቅት እንደተናገሩት ባንኩ በቴሌኮም ዘርፍ አለም አቀፍ ልምድ ካለው ድርጅት ጋር በጋራ ለመስራት እድል በማግኘቱ መደሰታቸውን በመግለፅ ሁለቱ ትላልቅ ድርጅቶች በስትራቴጂክ ጉዳዮች ላይ በመስራት በጋራ ተጠቃሚነታቸውን እንደሚያረጋግጡ ተናግረዋል።

13 Oct 2022

በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ስትራቴጂክ አጋርነት የተዘጋጀው 3ኛው ሀገር አቀፍ የሳይበር ደህንነት ወር የግንዛቤ ማስጨበጫ መርሃ ግብር እየተካሄደ ነው፡፡

በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ስትራቴጂክ አጋርነት እና በኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ አዘጋጅነት በተለያዩ ዝግጅቶች የሚከበረው ሶስተኛው የሳይበር ደህንነት ወር መርሃ ግብር ጥቅምት 1 ቀን 2015 ዓ.ም ተጀምሯል፡፡

05 Oct 2022

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከምስራቅ አፍሪካ ባንኮች በ3ኛ ደረጃ ተቀመጠ፡፡

አፍሪካን ቢዝነስ ባወጣው መረጃ መሰረት የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በ2022 ባስመዘገበው አፈፃፀም በ929 ሚሊዮን ዶላር ካፒታል ከምስራቅ አፍሪካ ባንኮች መካከል በ3ኛ ደረጃ ተቀምጧል፡፡

05 Oct 2022

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የኢሬቻ ክብረ በዓል ስፖንሰር በመሆኑ የተሰማውን ታላቅ ደስታ ገለፀ፡፡

ይህ የተገለፀው ባንኩ በፕላቲኒየም ደረጃ ስፖንሰር ያደረገው የኢሬቻ ክብረ በዓል አካል በሆነውና በስካይላይት ሆቴል በተከናወነው 2ኛው የቱሪዝም ሽልማት እና የሚስ ቱሪዝም ኦሮሚያ የቁንጅና ውድድር ዝግጅት ላይ ነው፡፡ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ ሱራ ሳቀታ በዝግጅቱ ላይ እንደገለፁት የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የኦሮሞ ሕዝብ ታላቅ የምስጋና በዓል የሆነው ኢሬቻ የ2015 ዓ.ም ክብረ በዓል አካል በመሆኑ ታላቅ ክብር ተሰምቶታል፡፡